የያዕቆብ መልዕክት ክፍል ፪
Semo Semo
523 subscribers
120 views
6

 Published On Sep 25, 2024

ቅዱስ ያዕቆብ እንደ አንድ ክርስትያን ገንዘብን፣ ሥልጣንን፣ የማኅበራዊ ኑሮ ሁኔታን ተመልክተን፣ የሰውን ፊት አይተን በማንም ላይ እንዳንፈርድ፣ የሰውን ልጅ ባልተገዛበት ምድራዊ ዋጋ እንዳንተምነው ያስጠነቅቀናል። በመሆኑም ቅዱስ ያዕቆብ እያንዳንዳችን የተገዛንበት፣ የተቤዥንበት ዋጋ ምን ያህል ታላቅ መሆኑን ያስታውሰናል። ቅዱስ ያዕቆብ በዚህ መልእክቱ ሁለት ሰዎችን በዐይናችን ፊት አስቀምጦ አስተያየታችንን እንድንፈትሽ ይጋብዘናል። የወርቅ ቀለበት ያጠለቀው እና ጌጠኛ ልብስ የለበሰው በአንድ ወገን፣ ድኃው እና መናኛ ልብስ የለበሰው በሌላ ወገን ሆነው ዋጋችን ስንት ነው ይላሉ! በዚህ ጥያቄ መሪነት ሰው የመሆንን ዋጋ የምንለካበትን ውኃ ልክ እንድናስተካክል፣ በምድራዊ መስፈርቶች የተንሸዋረረ እይታችንን እንድንገራ እንጋበዛለን።
መልካም ቆይታ!

show more

Share/Embed