ፈሪ ለጌታው | መልህቅ ፖድካስት
Tesfa Broadcasting Network  | GCME Tesfa Broadcasting Network | GCME
2.26K subscribers
3,897 views
177

 Published On Sep 28, 2024

አዳም በኃጢአት ከወደቀባት ቅጽበት አንስቶ አሁን እስካለንበት ዘመን ድረስ ክርስቲያን በብዙ ፈተና ውስጥ ያልፋል ። በኃጢአት በመውደቁ ምክንያት እግዚአብሔርን እንዳይቀርበው አድርጎት ከነበረው የዘር ኃጢአት (original sin) መድሃኒታችን በሆነው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል  ነፃ መሆን ችሏል ። ወደ ዘላለም ሞት ከሚወስደው የኃጢአት ዘር በደሙ ቢዋጅም ኃጢአት በማይነካው ማንነት መክበር ግን ገና በሰማይ ቀርቶለታል ። ይህም ማለት ስጋው በብዙ ምኞት ተከባ ስለምትኖር ተስፋ ወደ ተሰጠው የትንሳኤ አካል እስኪለወጥ ድረስ ከዚህች ከወደቀች ዓለም ፈተና መቅመሱ ግድ ነው። መፈተን ኃጢአት አይደለም፤ ነገር ግን ብዙውን ጊዜ ከሚያልፍባቸው የሰይጣን ፈተናና ማታለያ የተነሳ በኃጢአት ይወድቃል ። መውደቁ እግዚአብሔርን ባያስደስተውም አለተስፋ ግን አይተወውም እንዲድን ወድዶ ይታገሰዋል። የእግዚአብሔር ትዕግስት ግን በኃጢአት ልምምድ እንዲበረታ ዋስትና ሰጪ አይደለም።

በዛሬው ክፍል ስለ ስውር ኃጢአት እና የኃጢአት ልምምድ ተወያይተናል ይከታተሉን ።

show more

Share/Embed