ጠረንህን ላሽትተው - Terenihin Lashititew (Live Concert) || Rahel Wondwesen. New Amharic Mezmur 2013/2021
Rahel Wendwesen official Rahel Wendwesen official
23.9K subscribers
34,700 views
993

 Published On Jun 1, 2021

#EthiopianGosplesong

#Rahelwendwesenofficial

#Ethiopianmusic

#Protestantsong

#Ethiopianmezmure
“ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች።”
  — መዝሙር 42፥1

ሙቀት እንኳ ቢሆን እጅግም ቢወብቅ
ነፍሴን ይበርዳታል ከህልውናህ ውጭ
ግን ደግሞ ቅዝቃዜው በዝቶ በረዶ እንኳ ቢሆን
ነፍሴን ይሞቃታል በህልውናህ ውስጥ

ጠረንህን መዓዛህን ላሽትተው
መገኘትህን ህልውናህን ላሽትተው
የህይወቴ ተምኔት
በህልውናህ ሙቀት
በዚያ መቆየት

አንተ የሌለህበት አጀብ ግርግሩ
አይደንቃትም ነፍሴን እሱ አይደል ቁምነገሩ
ቅንጣት ባይኖራት መገኘትህ ግርምቷ
ፍስሀዋ ደምግባት ሳቅና ውበቷ

አሳ ከውሃ ወጥቶ እንደሚያቆም መኖር
የሞተ እንደሚባል ስሙ እንደሚቀየር
ጥገኛህ ነኝ ያላንተ የማልተነፍስ
የህይወቴ የመኖሬ ትርጉም ሙላኝ መንፈስቅዱስ

Original Song - Rahel Wedwesen

show more

Share/Embed