መዓዛህን እወደዋለው የዝማሬ አምልኮህብረት Original song Beti Tezera &Yosef Bekele New Ethiopian Amharic Mezmur 2020
Rahel Wendwesen official Rahel Wendwesen official
23.9K subscribers
1,231,369 views
9.9K

 Published On May 22, 2020

#EthiopianGosplesong

#Rahelwendwesenofficial

#Ethiopianmusic

#Protestantsong

#Ethiopianmezmure
ከስሬ ደርቼ ድሪቶዬን
ከላይ ብለብሰው የፀዳውን
ሰው እንደው የሚያየው ፊቴ ፊቴን
እከልላለሁ ገበናዬን (2x)

ግን አንተ አትዋሽም አትታለል
ዓይንህ ዘልቆ ልብን ያያል
ዓይንህ ዘልቆ ልብን ያያል (2x)

የቀድሞውን ፍቅር አጣሁት ፈልጌ
ኧረ እኔስ ፈራሁኝ ወዴት ነው ማደጊያዬ
ኧረ እኔስ ፈራሁኝ ወዴት ነው ማደጊያዬ
እግዚአብሔር ደጅ እንዳልጠናሁኝ
ዛሬማ ላፍታ እንኳ አቅም አጣሁኝ (2x)

ናፈቀኝ የጥንቱ ክብር
ናፈቀኝ ቤቴ የነበር
ናፈቀኝ ኦ እግዚአብሔር
ናፈቀኝ ረሃቤ ትጋቴ
ናፈቀኝ ትንሿ ዳሳዬ
ናፈቀኝ ያ ፀሎቴ

የተገለጠው ማንነቴ
ይኸው በፊትህ መድኃኒቴ
አቅም አጣሁኝ አግዘኝ
ያዘኝ ኃይልህን አልብሰኝ (2x)

ለአንተ ያለኝ ፍቅር ትኩስ የማይበርድ
በልቤ የሚኖር ሁል ጊዜ የሚነድ (2x)
መስሎኝ እንዳልነበር በልጅነቴ ወራት
ራሴን አገኘሁት ልምድ ሆኖብኝ ቃላት
ቤቴን አዘረፍኩት ከፍቼ ለጠላት

ናፈቀኝ ለቃልህ ያለኝ ቦታ
ናፈቀኝ ያ አሜን ያ እሽታ
ናፈቀኝ ኦ እርዳኝ ጌታ
ናፈቀኝ ለአንተ ያለኝ ክብር
ናፈቀኝ ሥምህ ሲነገር
ናፈቀኝ ኦ እግዚአብሔር

የተገለጠው ማንነቴ
ይኸው በፊትህ መድኃኒቴ
አቅም አጣሁኝ አግዘኝ
ያዘኝ ኃይልህን አልብሰኝ (2x)

ይልቅ ይልቅ ይቅርብኝ ልመልስ
ወደ ልብህ ወደ ሀሳብህ ልድረስ
ልሸከመው የመስቀልህን ፍቅር
ተመልሼ ወደ ኋላ እንዳልቀር
አድስልኝ የቀድሞውን ዘመን
ናፍቆት ሆኖ ምኞት ሆኖ እንዳይቀር
ሰምቼ አንተን እንዳፈራበት
ለም አድርገው የልቤን መሬት (2x)

show more

Share/Embed