ሕይወቴ አንተን ይምሰል Apostolic Church Ethiopia
ObeyActs Bible ObeyActs Bible
10.8K subscribers
7,313 views
107

 Published On Jun 26, 2019

ይሽተት ጠረኔ /አንተን አንተን ይበል/ 2*
ይቀየር መልኬ /አንተን ብቻ ይምሰል/ 2*
ለሚቀምሱኝ ኦሆ ለሚያሸቱኝ ኦሆ
አንተን አንተን እንድል
ይሽተት ጠረኔ አንተን አንተን ይበል
/ ይቀየር መልኬ አንተን ብቻ ይምሰል

1 በህይወቴ ልመስልህ ጓጓለሁ
ኑሮዬ እንዲያሳይህ እመኛለሁ
የፊት መልኬን ሳይሆን የውስጤን
ለውጠው ባክህ እኔነቴን

ላላወቁ አንተን ለሚሹ
መልክህን ሊያዩ ሚናፍቁ
በህይወቴ የሱስ እንዲያዩህ
ኑሮዬ አንተን ይምሰልህ

ውሎዬን ቃኘው በመንፈስ ቅዱስ
ሁሳቤም በቃልህ ኃይል ይፈወስ
ያክብርህ መውጣቴና መግባቴ
በ አረማመዴ ልምሰልህ አባቴ

ጠረኔ አንተን አንተን አንተን ይበል
ኑሮዬ አንተን አንተን አንተን ይምሰል
ህይወቴ አንተን አንተን አንተን ይምሰል
ውሎዬ አንተን አንተን አንተን ይምሰል

2 የተቀመመውን የዘይት ሽቱ
የሞቱ ዝንቦች እንዲያገሙት
ጠረኔን ሚያበላሽብኝን
ከህይወቴ ከኔ አርቅልኝ

አንተን አንተን እንድል ለሌሎች
በዙርያዬ ላሉት እንድመች
መንፈስህን አድስ እለት እለት
አድርሰኝ ወደ ፍፁም ሙላት

ይፍለቅ ፍቅርህ ዘወትር ከህይወቴ
ይብዛልኝ ፀጋ የሱስ አባቴ
ላንተ የሚመች ህይወት ሰጥተኸኝ
ባረማመዴም ምሳሌ አድርገኝ

ጠረኔ አንተን አንተን አንተን ይበል
ኑሮዬ አንተን አንተን አንተን ይምሰል
ህይወቴ አንተን አንተን አንተን ይምሰል
ውሎዬ አንተን አንተን አንተን ይምሰል
And be not conformed to this world: but be ye transformed by the renewing of your mind, that ye may prove what is that good, and acceptable, and perfect, will of God.Romans 12:2

show more

Share/Embed